በገዳ መሪዎች በኩል የተሰጠ የሥነ-ምግብ ትምህርት የሕፃናትን አመጋገብ አሻሽሏል - ጥናት
17:35 18.11.2026 (የተሻሻለ: 17:44 18.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በገዳ መሪዎች በኩል የተሰጠ የሥነ-ምግብ ትምህርት የሕፃናትን አመጋገብ አሻሽሏል - ጥናት
በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ የተካሄደ ጥናት ባህላዊ መሪዎች የሚሰጡት ሥነ-ምግብን የተመለከተ ትምህርት የሕፃናትን የምግብ ስብጥር እንደሚያሻሽል አሳይቷል።
የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጠውን ዝቅተኛ የምግብ ዓይነት ስብጥር ያሟሉ ሕፃናት ድርሻ በባሕላዊ የትምህርት ቡድን ከቁጥጥር ቡድኑ በእጥፍ የሚጠጋ ብልጫ አሳይቷል።
ማኅበረሰቡ የሚያምናቸውን ባህላዊ የአመራር መዋቅሮች ለጤና መልዕክት መጠቀም፣ ከመደበኛው አገልግሎት በተሻለ የሕፃናት ተጨማሪ ምግብ አመጋገብን እንደሚያጠናክር ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።
ጥናቱ በአኃዝ አስደግፎ ያቀረባቸውን ውጤቶች ለማግኘት የስፑትኒክ አፍሪካን የግራፊክስ ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X