ሊቢያ በደርና ከተማ ከ4 ሚሊዮን በላይ አደንዛዥ ዕዝ እንክብሎችን እንዲሁም 29 ኪሎ ግራም ኮኬይን እና ሃሺሽ በቁጥጥር ስር አዋለች
16:25 18.11.2026 (የተሻሻለ: 16:34 18.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሊቢያ በደርና ከተማ ከ4 ሚሊዮን በላይ አደንዛዥ ዕዝ እንክብሎችን እንዲሁም 29 ኪሎ ግራም ኮኬይን እና ሃሺሽ በቁጥጥር ስር አዋለች
በከተማዋ ሕገወጥ የዕፅ ዝውውር ሲፈጽሙ የነበሩ የወንጀል ቡድን አባላት መያዛቸውን በጄኔራል ሃፍታር የሚመራው የብሔራዊ መረጋጋት መንግሥት የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ዕፅ መከላከል ዋና አስተዳደር አስታውቋል።
አስተዳደሩ ይፋ ያደረጋቸው ፎቶግራፎች፣ የሃሺሽ ጥቅሎች ክምር፣ በነጭ እንክብሎች የተሞሉ ሳጥኖች እና ውስጣቸውን የሚያሳዩ ከረጢቶች ተደርድረው ያሳያሉ።
ይህ ዕፅ መያዙ የተሰማው፣ ሊቢያ ለአገር ውስጥ ተጠቃሚዎች እና በመላው አኅጉሪቱ ለሚገኙ ገበያዎች የሚታሰቡ ሰው ሠራሽ አደንዛዥ ዕፆች እና ሌሎች ሕገወጥ ዕፆች ዋና ቀጣናዊ ማጓጓዣ ማዕከል መሆኗን ባሳለፍንው ጥር ወር የተባበሩት መንግሥታት የዕፅ እና ወንጀል ቢሮ ሪፖርት ይፋ ካደረገ በኋላ ነው።
ከዚህ ቀደም በጄኔራል ሃፍታር የሚመራው የምሥራቃዊው የሊቢያ ብሔራዊ ሠራዊት አካል የሆነው "ሱቡል አል-ሰላም ብርጌድ" በኩፍራ 1.3 ሚሊዮን አደንዛዥ ዕፅ እንክብሎችን መያዙ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X