ግብርና፣ ኃይል፣ ቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ በሩስያ-አፍሪካ ትብብር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘፎች ናቸው - የግብፅ ባለሥልጣን

© telegram sputnik_ethiopiaግብርና፣ ኃይል፣ ቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ በሩስያ-አፍሪካ ትብብር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘፎች ናቸው - የግብፅ ባለሥልጣን
ግብርና፣ ኃይል፣ ቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ በሩስያ-አፍሪካ ትብብር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘፎች ናቸው - የግብፅ ባለሥልጣን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.11.2026
ሰብስክራይብ

ግብርና፣ ኃይል፣ ቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ በሩስያ-አፍሪካ ትብብር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘፎች ናቸው - የግብፅ ባለሥልጣን

በሩሲያ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማስፋት ግብርና፣ ኃይል፣ ቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አራት ዘርፎች መሆን እንዳለባቸው የግብፅ የመረጃ እና የውሳኔ ድጋፍ ማዕከል ኃላፊ ኦሳማ ኤል-ጎሃሪ በካይሮ በተከፈተው 4ኛው የቫልዳይ የውይይት ክበብ የሩስያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።

ክህሎት እና የአቅርቦት ሰንሰለት

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ረዳት የሆኑት ኤል-ጎሃሪ አክለውም፣ የኃይል ፕሮጀክቶች ለአፍሪካ መሐንዲሶች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠትን እንዲሁም ለሀገር ውስጥ አቅራቢዎች ዕድል መፍጠርን አብረው መያዝ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ምርምር እና ዲጂታል አስተዳደር

ባለሥልጣኑ የመስኖ ቅልጥፍናን፣ የውኃ አስተዳደርን እና የዲጂታል መንግሥት አገልግሎቶችን ለማሳደግ ከሩሲያ ጋር የጋራ ምርምር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

የጋራ ፋብሪካዎችን መገንባት እና ከአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ጋር ማስተሳሰር የጋራ የኢንዱስትሪ ተቋማትን ማቋቋም እና እነሱን ከአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ጋር ማስተሳሰር ገበያዎችን እንደሚያሰፋ እና በመላው አፍሪካ ያለውን የንግድ ትስስር እንደሚያጠናክርም ባለሥልጣኑ አክለው ገልጸዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተዘጋጀ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0