ናይጄሪያ፣ ካሜሩን፣ ቻድ እና ኒጀር ታጣቂ ቡድኖችን እስከ 5 ኪሎ ሜትር ድረስ ድንበር ተሻግሮ ለመዋጋት ተስማሙ
15:35 18.11.2026 (የተሻሻለ: 15:44 18.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ፣ ካሜሩን፣ ቻድ እና ኒጀር ታጣቂ ቡድኖችን እስከ 5 ኪሎ ሜትር ድረስ ድንበር ተሻግሮ ለመዋጋት ተስማሙ
ስምምነቱ ሽብርተኝነትን፣ የሽፍትነት ተግባራትን እና ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል መረቦችን ለመዋጋት የሚደረገውን ቀጣናዊ ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የናይጄሪያ መከላከያ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ሙሳ መናገራቸውን ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የናይጄሪያ ጦር በቅርቡ በሰሜን-ምሥራቅ እና በሰሜን-ምዕራብ አካባቢዎች ባደረጋቸው የሌሊት ዘመቻዎች በርካታ የታጣቂ እና የሽፍታ ቡድን መሪዎችን መግደሉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ይህ ስምምነት በተለይ በቦኮ ሃራም* እና በእስላማዊ መንግሥት የምዕራብ አፍሪካ ግዛት* ጋር በተያያዘ የፀጥታ መደፍረስ ለዓመታት በናይጄሪያ ድንበር አካባቢ ያሉ ማህበረሰቦችን ለጎዳው የካሜሩን የሩቅ ሰሜን ክልል ልዩ ፋይዳ አለው።
*ሩሲያን ጨምሮ በናይጄሪያ እና በሌሎች በርካታ ሀገራት በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X