በተመድ የሱዳን አምባሳደር አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫዎች እንደሚገባት ተናገሩ

ሰብስክራይብ

በተመድ የሱዳን አምባሳደር አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫዎች እንደሚገባት ተናገሩ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) እ.ኤ.አ በ1945 ሲመሠረት በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በቅኝ አገዛዝ ሥር ስለነበሩ፤ የአኅጉሪቱን ውክልና አሳንሷል ሲሉ አምባሳደር አል-ሀሪዝ ኢድሪስ አል-ሀሪዝ መሐመድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ቁልፍ ነጥቦች፦

◻ አፍሪካ የራሷ ጥንታዊ ሥልጣኔ ያላት እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ሰላም፣ ደኅንነት እና የምግብ ዋስትና ከፍተኛ አስተዋጽኦ የምታበረክት ታላቅ አኅጉር ናት።

◻ አኅጉሪቱ ያላትን ሚና በሚመጥን መልኩ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ቢያንስ ሁለት ቋሚ መቀመጫዎች እንዲሰጧት ትጠይቃለች።

◻ ሩሲያ በጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ዙሪያ አፍሪካ የያዘችውን አቋም በጽኑ ትደግፋለች።

◻ ሦስቱ ምዕራባውያን የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት ይህንን አቋም ለይስሙላ እንደግፋለን ቢሉም በተግባር ግን ተፈጻሚ ሲያደርጉት አይታይም።

◻ ይሁን እንጂ ግፊቱ እየተጠናከረ በመምጣቱ፤ በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ይፋዊ ውክልና ታገኛለች ብለው እንደሚጠብቁ ገልፀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0