የአፍሪካ የኒውክሌር ኃይል በሩሲያ ተንሳፋፊ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ሊጀምር ይችላል - የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ
የአፍሪካ የኒውክሌር ኃይል በሩሲያ ተንሳፋፊ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ሊጀምር ይችላል - የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ
አብዛኞቹ የአፍሪካ እና የደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀገራት ከሩሲያ ጋር የሚያደርጉትን የኒውክሌር ትብብር በተንሳፋፊ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ሊጀምሩ እንደሚችሉ የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሌክሲ ሊካቼቭ 'ሜድ ኢን ሩሲያ' በተሰኘው መድረክ ላይ መናገራቸውን የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
እንደ ሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ገለጻ፤ ጣቢያዎቹ ተመራጭ የሚሆኑባቸው ምክንያቶች፦
አጭር የግንባታ ጊዜ፣
አነስተኛና የታመቀ መጠን፣
ተመጣጣኝ ዋጋ።
አነስተኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች "ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሁሉም ድርድሮች ዋነኛ ትኩረት ሆነዋል" ያሉት ሊካቼቭ፤ እነዚህን ጣቢያዎች በብዛት የምታመርተውም ሆነ ተንቀሳቃሽ ተንሳፋፊ የኒውክሌር መፍትሔ በሥራ ላይ ያዋለችው ብቸኛዋ ሀገር ሩሲያ መሆኗን አክለዋል።
ሩሲያ ሦስተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ተከትሎ እነዚህን ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ለማድረግ ከግብፅ፣ ታንዛኒያ፣ ቶጎ፣ ናሚቢያ፣ ኡጋንዳ እና ጋና ጋር እየተወያየች መሆኗን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
የአፍሪካ ሀገራት ኢንዱስትሪ እና ግብርናቸውን ለማሳደግ አስተማማኝ የኃይል ምንጭ ስለሚያስፈልጋቸው፤ ወደ ሩሲያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ፊታቸውን ማዞር እንደጀመሩ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X