የጋምቢያ ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች ታኅሣሥ ከሚካሄደው ምርጫ አስቀድሞ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ
19:15 17.11.2026 (የተሻሻለ: 19:24 17.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የጋምቢያ ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች ታኅሣሥ ከሚካሄደው ምርጫ አስቀድሞ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ
አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት አዳማ ባሮው እና ሌሎች ሰባት ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች ሰኞ በባንጁል የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን የሀገሪቱ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።
▪ የቃል ኪዳኑ ይዘት፦
ሁሉም እጩዎች ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት እንዲረጋገጥ ለሰላም፣ ለመረጋጋት እና ለይፋዊው የዘመቻ የሥነ-ምግባር ደንብ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል። በምርጫ ኮሚሽኑ የተዘጋጀውን የፊርማ ሥነ-ሥርዓት የተመድ፣ የአፍሪካ ኅብረት እና የኢኮዋስ ተወካዮች ታድመውታል።
▪ እጩዎቹ፦
የምርጫ ኮሚሽኑ አዳማ ባሮውን፣ ዋነኛ ተቃዋሚ መሪዎች ኡሳይኑ ዳርቦ እና ታሊብ አህመድ ቤንሱዳን እንዲሁም ሦስት ነጻ እጩዎችን ጨምሮ የዘጠኝ ተወዳዳሪዎችን ዕጩነት አጽድቋል።
▪ የምርጫ ዘመቻ የጊዜ ሰሌዳ፦
ይህ ፊርማ እ.አ.አ ታኅሣሥ 5 ከሚካሄደው ምርጫ በፊት እስከ ታኅሣሥ 3 ድረስ የሚቆየውን የቅስቀሳ ዘመቻ በይፋ አስጀምሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X