ናይጄሪያ የዓለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ምክር ቤት መቀመጫን በድጋሚ አገኘች - ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት

© telegram sputnik_ethiopiaናይጄሪያ የዓለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ምክር ቤት መቀመጫን በድጋሚ አገኘች - ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት
ናይጄሪያ የዓለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ምክር ቤት መቀመጫን በድጋሚ አገኘች - ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.11.2026
ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ የዓለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ምክር ቤት መቀመጫን በድጋሚ አገኘች - ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት

ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ ሀገራቸው እ.ኤ.አ ከ2027 ጀምሮ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ለአዲስ የሥራ ዘመን ለምክር ቤቱ መመረጧን "ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ እና ስትራቴጂካዊ ድል" ሲሉ ማወደሳቸውን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የምርጫው አንደምታ

የተጠናከረ ዓለም አቀፍ ሚና፦ አዲሱ ኃላፊነት ናይጄሪያ በዓለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ የዲጂታል ፈጠራ እና የኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር ውስጥ ያላትን ሚና ይበልጥ ያጠናክራል።

ለታዳጊ ሀገራትን ጥቅም መሟገት፦ ናይጄሪያ በተባበሩት መንግሥታት ልዩ ኤጀንሲ ውስጥ ያላትን መቀመጫ ተጠቅማ፤ ለታዳጊ ሀገራት ፍላጎት እንደምትሟገትና አካታች ዓለም አቀፍ ዲጂታል ሽግግርን እንደምታበረታታ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

በዶሃ የተገኘው ዲፕሎማሲያዊ ስኬት፦ ፕሬዚዳንቱ በኳታር ዶሃ በተካሄደው የዓለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ጉባኤ፤ በመገናኛ ብዙኃን ሚኒስትር ቦሱን ቲጃኒ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቢያንካ ኦዱሜግዉ-ኦጁክዉ መሪነት የተሳካ ዲፕሎማሲያዊ ሥራ ለሠሩት የናይጄሪያ ጉባኤ አባላት ምሥጋና አቅርበዋል።

ዓለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ምክር ቤት በየአራት ዓመቱ በሚደረግ ምርጫ ከሚመረጡ 48 አባል ሀገራት የተዋቀረ ሲሆን ስትራቴጂካዊ እቅዶችን፣ በጀቶችን እና ዓለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ፖሊሲዎችን ለመምራት በየዓመቱ ይሰበሰባል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0