የሩሲያ ኤሮስፔስ ኃይሎች አዲስ የሱ-34 ተዋጊ ጀቶችን ተረከቡ
17:25 17.11.2026 (የተሻሻለ: 17:34 17.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኤሮስፔስ ኃይሎች አዲስ የሱ-34 ተዋጊ ጀቶችን ተረከቡ
ጀቶቹ ሙሉ የምድር እና የአየር የሙከራ ሂደቶችን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀው ለስምሪት መላካቸውን መንግሥታዊው ኮርፖሬሽን ሮስቴክ አስታውቋል።
ቁልፍ ዝርዝሮች፦
ድርብ አቅም፦ የሱ-34 አውሮፕላን የተዋጊ እና የቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን አቅም በማቀናጀት የምድር፣ ውኃ እና የአየር ኢላማዎችን መምታት ይችላል።
የውጊያ አቅም፦ ጀቶቹ በውስብስብ የአየር ሁኔታዎች እና የጠላት የአየር መከላከያ ሥርዓት እርምጃዎች መካከል ተልዕኮ ለመፈጸመ የተነደፉ ናቸው።
የምርት ፍጥነት፦ የሮስቴክ ድርጅቶች ወታደራዊ መሣሪያዎችን ያለማቋረጥ እና በታቀደው ፍጥነት ለማድረስ የምርት ሂደቶቻቸውን ያለማቋረጥ እያሻሻሉ ይገኛሉ።
የተረጋገጠ አፈጻጸም፦ ሱ-34 ከፍተኛ የጥቃት ኃይል፣ ረጅም የበረራ ርቀት እና አስተማማኝነት ማሳየቱን የጠቆመው መንግሥታዊው ኮርፖሬሽን፤ የኤሮስፔስ መሐንዲሶች የቴክኒክ ባህሪያቱን ማሻሻላቸውን እንደሚቀጥሉ አፅንኦት ሰጥቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X