አምስት የአውሮፓ ሀገራት ከ2027 መጀመሪያ አንስቶ በሩዋንዳ የስደተኞች ማቆያ ማዕከል ሊያቋቋሙ ይችላሉ - መገናኛ ብዙኃን

© telegram sputnik_ethiopiaአምስት የአውሮፓ ሀገራት ከ2027 መጀመሪያ አንስቶ በሩዋንዳ የስደተኞች ማቆያ ማዕከል ሊያቋቋሙ ይችላሉ - መገናኛ ብዙኃን
አምስት የአውሮፓ ሀገራት ከ2027 መጀመሪያ አንስቶ በሩዋንዳ የስደተኞች ማቆያ ማዕከል ሊያቋቋሙ ይችላሉ - መገናኛ ብዙኃን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.11.2026
ሰብስክራይብ

አምስት የአውሮፓ ሀገራት ከ2027 መጀመሪያ አንስቶ በሩዋንዳ የስደተኞች ማቆያ ማዕከል ሊያቋቋሙ ይችላሉ - መገናኛ ብዙኃን

ጀርመን፣ ኔዘርላንድስ፣ ግሪክ፣ ኦስትሪያ እና ዴንማርክ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ለተደረገባቸው ስደተኞች ማቆያ የሚሆን ማዕከል በኪጋሊ ለማቋቋም ከሩዋንዳ መንግሥት ጋር መነጋገር መጀመራቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

▪ ዋና ዓላማ፦ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያላገኙ ግለሰቦች ወደ መጡበት ሀገር እስኪመለሱ ድረስ በጊዜያዊነት ማቆየት።

▪ ሁኔታዎች፦ ስደተኞቹ በዚህ ማዕከል ቆይታ ካደረጉ በኋላ ሕይወታቸውን በሩዋንዳ እንደገና መገንባት፣ በፈቃደኝነት ወደ መጡበት ሀገር መመለስ ወይም የመኖርያ ፈቃድ ወዳገኙበት ሌላ ሀገር መሄድ ይችላሉ።

▪ የጊዜ ሰሌዳ፦ ከሩዋንዳ ጋር የሚደረገው ስምምነት መጨረሻ ሲያገኝ፤ የመጀመሪያዎቹ ስደተኞች ዝውውር እ.ኤ.አ በ2027 ሊጀመር ይችላል።

▪ ምላሾች፦ የኦስትሪያ ቻንስለር ክርስቲያን ስቶከር ይህንን ተነሳሽነት "ለስደተኞች ፖሊሲ እጅግ ታሪካዊ ለውጥ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን የአውሮፓ ኅብረት የመሠረታዊ መብቶች ኤጀንሲ ግን የተጎጂዎችን መብቶች ሙሉ በሙሉ ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስቧል።

እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ፤ የፕሮጀክቱ ሕጋዊ እና ተግባራዊ አፈጻጸም ዝርዝሮች አሁንም በድርድር ላይ ይገኛሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0