ኮትዲቯር ጦሯን ወደ ሄይቲ ልትልክ ነው

© telegram sputnik_ethiopiaኮትዲቯር ጦሯን ወደ ሄይቲ ልትልክ ነው
ኮትዲቯር ጦሯን ወደ ሄይቲ ልትልክ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.11.2026
ሰብስክራይብ

ኮትዲቯር ጦሯን ወደ ሄይቲ ልትልክ ነው

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በዓለም አቀፉ የፍራንኮፎኒ ድርጅት ድጋፍ በአቢጃን ሥልጠና የወሰደው የኮትዲቯር ጦር ሻለቃ፤ ዝግጅቱን ባሳለፍነው መስከረም ወር ማጠናቀቁን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

812 ወታደሮች በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ለስድስት ወራት ተልዕኮ የጸደቀውን ፀረ-ወንበዴ ኃይል ይቀላቀላሉ።

ወደ 100 የሚጠጉ ወታደራዊ አባላትን የያዘ የቅድመ ዝግጅት ቡድን ቀደም ብሎ ሕዳር 14 ፖርት-ኦ-ፕሪንስ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። ዋናው የጦር ክፍል ደግሞ ሕዳር መጨረሻ አልያም ታህሳስ መጀመሪያ ላይ ይደርሳል ተብሏል።

ዋና ዋና ዓላማዎች፦

የታጠቁ ወንበዴ ቡድኖችን መዋጋት፣

ከሄይቲ ፖሊስ እና ጦር ጋር በመቀናጀት ወደቦችና ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎችን መጠበቅ፣

ከሲቪል ዜጎች ጋር የሚደረገውን ግንኙነት ለማቀላጠፍ የሄይቲ ክሪዮል ቋንቋ ሥልጠና መውሰድ።

ከ150 እስከ 200 ከሚደርሱ ታጣቂ ቡድኖች ጋር እየተዋጋ የሚገኘው የፀረ-ወንበዴ ኃይል፤ የታቀደውን 5,500 የሰው ኃይል ቁጥር ለማሟላት እንደተቸገረ ተገልጿል።

በሄይቲ የሚገኘው የተመድ ጥምር ኃይል ጽሕፈት ቤት ባወጣው መረጃ መሠረት፤ ከሐምሌ እስከ መስከረም 2026 ባለው ጊዜ ውስጥ ሪፖርት ከተደረጉት 1,167 ሞቶች መካከል ከ45% በላይ ለሚሆኑት ተጠያቂዎቹ ታጠቂ የወንበዴ ቡድኖች ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopiaኮትዲቯር ጦሯን ወደ ሄይቲ ልትልክ ነው
ኮትዲቯር ጦሯን ወደ ሄይቲ ልትልክ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.11.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0