- Sputnik አፍሪካ, 1920
የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ 2026
3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በኢኮኖሚያዊ እና ሰብዓዊ ትብብር ላይ በማተኮር ጥቅምት 18 እና 19 ቀን 2019 ዓ.ም. በሞስኮ ይካሄዳል። በመንግሥታት መካከል ስምምነቶችን መፈፀም እና የንግድ ውሎችን መፈረም የጉባኤው አጀንዳ ናቸው።

ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ፦ ከጉባኤው ምን ይጠበቃል?

© telegram sputnik_ethiopiaሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ፦ ከጉባኤው ምን ይጠበቃል?
ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ፦ ከጉባኤው ምን ይጠበቃል? - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.10.2026
ሰብስክራይብ
ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ፦ ከጉባኤው ምን ይጠበቃል?

ጥቅምት 18 እና 19 ሞስኮ ከፍተኛ መሪዎችና ፖሊሲ አውጪዎች ኢኮኖሚ፣ ኢንቨስትመንት እና ሰብዓዊ ትብብርን ጨምሮ በቁልፍ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክሩበትን ከፍተኛ ጉባኤ ታስተናግዳለች።

ከ46 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ከ200 በላይ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የጉባኤው ዓላማዎች እና የሚጠበቁ ውጤቶች፦

ዋነኛው የሚጠበቀው ውጤት እ.ኤ.አ በ2023 የተዘረጋውን ማዕቀፍ የሚተካ አዲስ የ2027–2029 የሩሲያ-አፍሪካ የድርጊት መርኃ-ግብር ማጽደቅ ነው።

በተጨማሪም የአፍሪካ መገናኛ ብዙኃን ተወካዮች በርካታ ስምምነቶች ይፈረማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቀድመው ጠቁመዋል።

የፕሮግራሙ ዋና ዋና መርኃ-ግብሮች፦
የተለያዩ ውይይቶች እና የክብ ጠረጴዛ ስብሰባዎች፣
የባለብዙ ወገን እና የሁለትዮሽ ስብሰባዎች፣
በፕሬዚዳንት ፑቲን እና በአፍሪካ መሪዎች መካከል የሚደረጉ በርካታ የሁለትዮሽ ውይይቶች፣
የእግር ኳስ ጨዋታን ጨምሮ ባሕላዊ እና ስፖርታዊ መርኃ-ግብሮች።

ሁለተኛው ጉባኤ ምን አሳካ?

ሁለተኛው ጉባኤ በ2023 በሴንት ፒተርስበርግ የተካሄደ ሲሆን ከ160 በላይ ይፋዊ ስምምነቶች ተፈርመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0