- Sputnik አፍሪካ, 1920
የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ 2026
3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በኢኮኖሚያዊ እና ሰብዓዊ ትብብር ላይ በማተኮር ጥቅምት 18 እና 19 ቀን 2019 ዓ.ም. በሞስኮ ይካሄዳል። በመንግሥታት መካከል ስምምነቶችን መፈፀም እና የንግድ ውሎችን መፈረም የጉባኤው አጀንዳ ናቸው።

ሩሲያ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ውጥረቶች በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ውጥረቶች በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች
ሩሲያ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ውጥረቶች በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.10.2026
ሰብስክራይብ
ሩሲያ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ውጥረቶች በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

ይህ የተገለጸው በሞስኮ ከሚካሄደው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ እና በሩሲያ ፌዴሬሽን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆርጂ ቦሪሰንኮ መካከል በተካሄደው ውይይት ነው።

በውይይቱ በሩሲያና ኢትዮጵያ መካከል በኢኮኖሚ፣ በሳይንስና ቴክኒክ ትብብር እንዲሁም በንግድ ዘርፎች የሚከናወኑ መንግሥታዊ ሥራዎችን ማስቀጠል እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።

ሁለቱ ወገኖች የፖለቲካ ውይይት ለማጠናከርና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ መድረኮች የአቋም ቅንጅታቸውን ለማሳደግ ቁርጠኛ እንደሆኑም አረጋግጠዋል።

የሩሲያ ወገን በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በሰጠው አስተያየት፤ በቀጣናው ሀገራት መካከል ያሉ ግጭቶች የዓለም አቀፍ ሕግ መርሆችን መሠረት በማድርግ፤ በፖለቲካዊ ውይይትና በዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ብቻ መፍታት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0