ግብፅ፣ አልጄሪያና ቱኒዚያ ለሊቢያ መራሽ የፖለቲካ መፍትሔ ድጋፋቸውን አረጋገጡ
08:45 27.10.2026 (የተሻሻለ: 08:54 27.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ግብፅ፣ አልጄሪያና ቱኒዚያ ለሊቢያ መራሽ የፖለቲካ መፍትሔ ድጋፋቸውን አረጋገጡ
የግብፅ፣ አልጄሪያና ቱኒዚያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአልጄሪያ ባካሄዱት የሊቢያ ጎረቤት ሀገራት ሦስትዮሽ ትብብር ማዕቀፍ የሚኒስትሮች ስብሰባ በሀገሪቱ ጉዳይ አቋማቸውን ስለማቀናጀት መክረዋል።
ሚኒስትሮቹ የሚከተሉትን ጥሪዎች አቅርበዋል፦
▪ የሊቢያን አንድነት ለሚጠብቅና የመንግሥት ተቋማትን ለሚያዋህድ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ መፍትሔ፣
▪ የተጓተተው የሽግግር ሂደት መጨረሻ እንዲያገኝ የፕሬዚዳንታዊና የፓርላማ ምርጫዎችን በተቻለ ፍጥነት
አንድ ላይ ማካሄድ፣
▪ በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔዎች መሠረት የውጭ ኃይሎች፣ ቅጥረኞችና የውጭ ተዋጊዎችን ከሊቢያ በአፋጣኝ ማስወጣት፣
▪ የፖለቲካ፣ ደኅንነት፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች መንስኤዎችን ለመፍታት ሁሉን አቀፍ አካሄድ መከተል፣
▪ የሊቢያ የተፈጥሮ ሀብቶችና በውጭ ሀገራት የታገዱ የገንዘብ ሀብቶች ጥበቃ እንዲጠናከር እንዲሁም ሀብቶቹ በአግባቡ እንዲተዳደሩና ለሊቢያ ሕዝብ ጥቅም እንዲውሉ ማድረግ።
ሦስቱ ሀገራት በተባበሩት መንግሥታት ድጋፍ ሥር የሚንቀሳቀሱ የሊቢያ ጎረቤት ሀገራት፤ በፖለቲካ ሂደቱ እና የሀገሪቱን ተቋማት ክፍፍል በማስቆም ረገድ የሚጫወቱትን ቁልፍ ሚና አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
