ቻይና በአፍሪካ ለተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች አራት የሰላም መፍትሄ መርሆዎችን አቀረበች
08:02 26.10.2026 (የተሻሻለ: 08:04 26.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቻይና በአፍሪካ ለተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች አራት የሰላም መፍትሄ መርሆዎችን አቀረበች
በዚህ ወር በቻይናና በቶጎ መሪዎች መካከል በተካሄደ ስብሰባ የቀረበው ማዕቀፍ፤ በአፍሪካ የሚከሰቱ ግጭቶችን መፍታት ላይ ያተኮሩ አራት ዋና ዋና መርሆዎችን እንዳስቀመጠ ሳውዝ ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል።
ከውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነና አፍሪካ መር የደህንነት መፍትሄ።
የሀገራትን ሉዓላዊነት እና በተባበሩት መንግሥታት ቻርተር የተቀመጡ መርሆዎችን ማክበር።
ከኃይልና የተናጠል ማዕቀቦች ይልቅ፤ በውይይት ላይ የተመሠረቱ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ማበረታታት።
አስቸኳይ የደህንነት ችግሮችን ከመፍታት ጎን ለጎን ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ።
ይህ የቻይና የሰላም ማዕቀፍ በድንበር አካባቢ ትንኮሳና በትግራይ ክልል የተወካይ ኃይሎችን በመደገፍ ለሚካሰሱት ኢትዮጵያና ኤርትራ ወቅታዊ ውጥረት ተፈጻሚ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X