በኮፕ 32 ጉባኤ ወቅት የኃይል መቆራረጥ እንዳይኖር 18 ፕሮጀክቶች በይፋ ተጀምረዋል- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
10:03 25.10.2026 (የተሻሻለ: 10:04 25.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኮፕ 32 ጉባኤ ወቅት የኃይል መቆራረጥ እንዳይኖር 18 ፕሮጀክቶች በይፋ ተጀምረዋል- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዓመት 2020 ዓ.ም ሕዳር ወር ለምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) አስተማማኝና ዘመናዊ የኃይል አቅርቦት ለማረጋገጥ 18 ፕሮጀክቶች መጀመራቸውን አገልግሎቱ አስታውቋል።
ከተጀመሩት ፕሮጀክቶች መካከል ሦስቱ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ሲሆኑ ሁለቱ ተንቀሳቃሽ ጣቢያዎች እና አንደኛው በአዲስ አበባ የሚገነባ ቋሚ ማከፋፈያ ጣቢያ ነው።
ፕሮጀክቶቹ በአዲስ አበባ፣ ሸገር እና አዳማ ከተሞች የሚተገበሩ ሲሆን የትራንስፎርመሮችን አቅም የመጨመር፣ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን የመዘርጋትና የመሬት ውስጥ የኃይል መስመሮችን የማደራጀት ሥራዎችን ያካትታሉ።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X