የሩሲያ የባሕር ኃይል መርከብ በናሚቢያ ወታደራዊ አቅሟን እና የካዴቶች ሥልጠና ሂደትን አሳየች - ኤምባሲ
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ የባሕር ኃይል መርከብ በናሚቢያ ወታደራዊ አቅሟን እና የካዴቶች ሥልጠና ሂደትን አሳየች - ኤምባሲ
'ፔረኮፕ' የተሰኘችው የሩሲያ የሥልጠና መርከብ በዋልቪስ ቤይ ወደብ ወዳጃዊ ጉብኝት ማድረጓን በናሚቢያ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል።
በጉብኝቱ ወቅት የሩሲያ የባሕር ኃይል አዛዦች ከናሚቢያ የባሕር ኃይል አመራሮች ጋር የተገናኙ ሲሆን የመርከቧን የውጊያ አቅም እንዲሁም የሩሲያ እና ናሚቢያ ካዴቶች የጋራ ሥልጠና ሂደት ማሳየታቸውን ኤምባሲው ገልጿል።
ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ፣ የቆየ ወዳጅነት እና መከባበር የሚያጎላ መሆኑን ኤምባሲው አስምሮበታል።
ፔረኮፕ ቀደም ሲል የሞዛምቢክ፣ ሴይሼልስ እና ታንዛኒያ ወደቦችን መጎብኘቷ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X