የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በዚምቧቤ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲነሱ ጠየቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በዚምቧቤ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲነሱ ጠየቀ
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በዚምቧቤ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲነሱ ጠየቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.10.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በዚምቧቤ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲነሱ ጠየቀ 

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፤ በዚምቧቤ ላይ የተጣሉ የተናጠል ማዕቀቦች በአፋጣኝ እንዲነሱ ኅብረቱ ለረጅም ጊዜ ሲጎተጉት የቆየውን ጥያቄ እንደገና አቅርበዋል። ማዕቀቦቹ በሀገሪቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል። 

ዋና ዋና ነጥቦች፦ 

ማዕቀቦቹ ዚምቧቤ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓቶችን እንዳትጠቀም እንቅፋት ከመሆናቸው ባሻገር፤ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን እንዲገደብ እና የንግድ ሥራ ማስኬጃ ወጪዎች እንዲጨምሩ አድርገዋል። 

እርምጃዎቹ የልማት ድጋፎችን፣ የዚምቧቤን ራዕይ 2030፣ ክልላዊ የውህደት ግቦችን፣ የአፍሪካ ኅብረት አጀንዳ 2063ን እና የተባበሩት መንግሥታት ዘላቂ የልማት ግቦችን ያደናቅፋሉ። 

የአፍሪካ ኅብረት ዚምቧቤ ማዕቀቦቹ እንዲነሱ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጧል። ኅብረቱ በዚህ ጉዳይ ከደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ ጋር ተመሳሳይ አቋም መያዙን ገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0