ኪየቭ የሰላም ስምምነት በማዘግየት ከፍተኛ ዋጋ ትከፍላለች - አሜሪካዊ ባለሙያ
10:24 23.10.2026 (የተሻሻለ: 10:34 23.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኪየቭ የሰላም ስምምነት በማዘግየት ከፍተኛ ዋጋ ትከፍላለች - አሜሪካዊ ባለሙያ
በኪየቭ እና በአውሮፓ በኩል ጊዜ ከጎናቸን ነው የሚል እምነት ቢኖርም፤ የዩክሬን የመደራደር አቅም በፍጥነት እየተዳከመ መሆኑን በዲፌንስ ፕራዮሪቲስ የምርምር ማዕከል የወታደራዊ ትንተና ዳይሬክተር ጄኒፈር ካቫናግ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ለዚህም ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች ጠቅሰዋል፦
ስትራቴጂካዊ መሠረተ ልማቶችን የመከላከል አቅም እየተዳከመ መምጣቱ፣
ሙሉ በሙሉ በአውሮፓ ሊሸፍን የማይችል የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ፣
በዘለንስኪ ሕጋዊነት ላይ እየጨመሩ የመጡ ጥያቄዎች።
ወደፊት የሚደረግ የትኛውም የሰላም ስምምነት ባለፈው መጋቢት 2025 ትራምፕ ሥልጣን ከተረከቡ በኋላ ሊደረግ ከሚችለው ስምምነት አንፃር ለዩክሬን በጣም የከፋ እንደሚሆን ካቫናግ ደምድመዋል።
ይህ አዘቅት ውስጥ የመግባት ሂደት ከአሜሪካ ጋር በተፈጠረው የሻከረ ግንኙነት የተነሳ የበለጠ እየተባባሰ መጥቷል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ዘለንስኪ ግጭቱን ለማቆም ፍላጎት የለውም ሲሉ በመተቸት፤ ከሞስኮ ጋር ስምምነት መፍጠር የሚችል አዲስ መሪ ዩክሬን እንደሚያስፈልጋት ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X