የአፍሪካ የመረጃ ሥርዓት ተናባቢ አይደለም - የአፍሪካ ኅብረት ስታቲስቲክስ ኢንስቲትዩት
09:53 23.10.2026 (የተሻሻለ: 09:54 23.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ የመረጃ ሥርዓት ተናባቢ አይደለም - የአፍሪካ ኅብረት ስታቲስቲክስ ኢንስቲትዩት
በሌሎች የመረጃ ምንጮች ላይ ጥገኛ መሆንን ለማስቀረት የአፍሪካ ሀገራት ብሔራዊ የስታትስቲክስ ቢሮዎች በመረጃ ሉዓላዊነት ላይ እየሠሩ እንደሆነ የአፍሪካ ኅብረት ስታቲስቲክስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አዱም ጋጎሉም ከ10ኛው የአፍሪካ የስታቲስቲክስ ኮሚሽን ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
የመረጃ ሉዓላዊነት፦ አፍሪካ የራሷ መረጃ ሊኖራት ይገባል፤ “የራሳችንን የስታቲስቲክስ ሥራዎች በራሳችን መደገፍ እንፈልጋለን።”
ተናባቢ የመረጃ ሥርዓት፦ በአፍሪካ የመረጃ አያያዝ የተበታተነና ከፍተኛ ክፍተት ያለበት በመሆኑ፤ ይህንን ለመቅረፍ እና ሉዓላዊ የመረጃ ሶፍትዌሮች ለመዘርጋት እየተሠራ ነው።
የአፍሪካ ኅብረት የመዋጮ ግዴታ፦ እ.አ.አ 2019 የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ አባል ሀገራት ከብሔራዊ በጀታቸው 0.15% ለስታቲስቲክስ ሥራዎች እንዲመድቡ ያስተላለፈውን ውሳኔ እየተገበሩ ያሉት 16 ሀገራት ብቻ ናቸው።
“እንደ አፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ያሉ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ለማሳካትና የአፍሪካን ንግድ ለማሳደግ ስለአፍሪካ ንግድ የሚገልጽ አፍሪካዊ መረጃ ያስፈልገናል።”
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X