አስተማማኝ የመረጃ እና የስታቲስቲክስ ስርዓት መገንባት ለአፍሪካ ዘላቂ ዕድገት ወሳኝ ነው - ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
10:24 22.10.2026 (የተሻሻለ: 10:34 22.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አስተማማኝ የመረጃ እና የስታቲስቲክስ ስርዓት መገንባት ለአፍሪካ ዘላቂ ዕድገት ወሳኝ ነው - ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
ፕሬዚዳንቱ ጥሪውን ያቀረቡት ረቡዕ አዲስ አበባ ውስጥ ተካሄዶ በነበረው 10ኛው የአፍሪካ የስታቲስቲክስ ኮሚሽን ጉባኤ እና 12ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ጂኦስፓሻል መረጃ አስተዳደር ክልላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው።
የርዕሰ ብሔሩ ጥሪዎች፦
▪ የአፍሪካ ሀገራት ብሔራዊ የስታቲስቲክስ ስርዓቶቻቸውን እንዲያጠናክሩ፣
▪ የይፋዊ መረጃዎችን ገለልተኝነት እንዲጠብቁ፣
▪ የልማት ፖሊሲዎቻቸውን በሚታመኑ መረጃዎች ላይ እንዲመሰርቱ።
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሥራ አስፈጻሚ ክላቨር ጋቴቴ በበኩላቸው፤ አፍሪካ ለዘመናዊ የስታቲስቲክስ መሠረተ ልማቶች ግንባታ እና ለመረጃዎች ጥራት ትኩረት እንድትሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X