የሩሲያና የቻይናን የሕግ ትብብር የላቀ ደረጃ የሚያደርስ ሁሉን አቀፍ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል — የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ

የሩሲያና የቻይናን የሕግ ትብብር የላቀ ደረጃ የሚያደርስ ሁሉን አቀፍ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል — የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ
ኢጎር ክራስኖቭ ይህን ያሉት ከቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የፍትሕ ሚኒስትር ሄ ሮንግ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።
በውይይቱ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
የሩሲያና የቻይና ግንኙነት በቭላድሚር ፑቲንና ሺ ጂንፒንግ መሪነት ጠንካራ መሠረት ያለውና በፍጥነት እያደገ የሚገኝ ነው።
የኢኮኖሚና የሰብዓዊ ግንኙነቶች መጠናከር የአስተማማኝ የሕግ መዋቅር አስፈላጊነትን አሳድጓል።
በሁለቱ ሀገራት ለሥራ የሚሠማሩ ዜጎችና ድርጅቶች መብቶቻቸው አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ እንደሚጠበቅ እርግጠኛ መሆን አለባቸው። ይህም የፍርድ ቤቶች፣ የፍትሕ ተቋማትና የሁሉም የሕግ ተቋማት የጋራ ኃላፊነት ነው።
ክራስኖቭ፤ “ችግሩ ሕግን ማውጣት ሳይሆን፣ በጥብቅ መተግበሩን ማረጋገጥ ነው” የሚለውን የቻይናዊውን የፖለቲካ ሰው ዣንግ ጁዝንግን ንግግር ጠቅሰዋል።
ተስፋ ሰጪ የትብብር መስኮች
ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች
የቻይና የፍትሕ ሚኒስቴር በየቀኑ ለ24 ሰዓታት የሕግ ድጋፍ ለማቅረብ የተቀናጁ ቢሮዎችን፣ የስልክ ማዕከልንና የመስመር ላይ አገልግሎቶችን እያስፋፋ ሲሆን ሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ ብሎክቼይንና ግዙፍ የመረጃ ትንተናን በመጠቀም ላይ ይገኛል።
በሩሲያ፤ ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በፍርድ ሥራዎች ውስጥ ለማስተዋወቅ የሚያስችል ጽንሰ ሐሳባዊ ማዕቀፍ ጸድቋል። ማዕቀፉ ኒውራል ኔትወርኮች ጥቅም ላይ በሚውሉበት ወቅት የሰው ልጆች መብትና ነፃነቶች እንዲጠበቁ የሚያረጋግጡ ድንጋጌዎችን ያካትታል።
ሳይንስና ትምህርት
በግንቦት ወር በቤጂንግ የሩሲያና የቻይና የትምህርት ትብብር ዓመት ተጀምሯል።
በሌቤዴቭ ስም የተሰየመው የሩሲያ የፍትሕ ስቴት ዩኒቨርሲቲም ከቻይና የፍትሕ ሚኒስቴር ልዩ ተቋማት ጋር ትብብሩን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
“ሁሉን አቀፍ አካሄድ የሩሲያና ቻይናን የሕግ ትብብር ሥርዓታዊና እንከን የለሽ ወደሆነ አሠራር ለማሸጋገር ያስችላል” ሲሉ ኢጎር ክራስኖቭ አጠቃለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X