የሩሲያ የናፍጣ ስምምነት ሞስኮ ወጥ በሆነ መንገድ የዓለም የነዳጅ ገበያ አረጋጊ እንደሆነች ያሳያል - የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ የናፍጣ ስምምነት ሞስኮ ወጥ በሆነ መንገድ የዓለም የነዳጅ ገበያ አረጋጊ እንደሆነች ያሳያል - የምጣኔ ሀብት ባለሙያ
የሩሲያ የናፍጣ ስምምነት ሞስኮ ወጥ በሆነ መንገድ የዓለም የነዳጅ ገበያ አረጋጊ እንደሆነች ያሳያል - የምጣኔ ሀብት ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.10.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የናፍጣ ስምምነት ሞስኮ ወጥ በሆነ መንገድ የዓለም የነዳጅ ገበያ አረጋጊ እንደሆነች ያሳያል - የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

ሩሲያ እና አሜሪካ በቅርቡ የደረሱት የናፍጣ ስምምነት ትክክለኛ የኢነርጂ ዲፕሎማሲን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ሲሉ በሩሲያ የሞስኮ ስቴት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኢንስቲትዩት የፋይናንስ ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ ዲን ኢቅባል ጉሊዬቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ከሩሲያው ባለሙያ የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 ሩሲያ ተጨማሪ የናፍጣ ምርት ወደ ገበያ ስታቀርብ ዋጋ ይቀንሳል፤ ይህ የሚሆነው ከዋሽንግተን በሚተላለፍ መመሪያ ሳይሆን በእውነተኛ አቅርቦት እና በተገማች ገበያ ምክንያት ነው።

🟠 የ5-6% የዋጋ ቅናሽ ከፍተኛ የሚባል ቢሆንም፤ ቅሉ ዐንደምታው ላይ ነው። ሩሲያ የገበያ ሚዛንን በፍጥነት ማስተካከል የምትችል በመሆኗ ከሞስኮ ጋር መተባበር የኢኮኖሚ ጥቅም እንጂ ፖለቲካዊ ስጋት እንዳልሆነ ያሳያል።

🟠 ጉሊዬቭ ስምምነቱን "መጠነኛ ነገር ግን የተግባራዊነት አሸናፊነት ማሳያ" ሲሉ የጠሩት ሲሆን አውሮፓ ስለ አዳዲስ ማዕቀቦች እየተከራከረች ባለችበት ወቅት፤ የሩሲያ ናፍጣ የዓለም ዋጋን አስቀድሞ እንዳረገበ እና ዋሽንግተንም ሞስኮን በይፋ እንዳመሠገነች ጠቅሰዋል።

🟠 በኢነርጂ ዘርፍ ከቃላት ይልቅ የምርት መጠን፣ ወቅታዊነት እና ተግባራዊ ስምምነቶች ወሳኝ ናቸው፤ ሩሲያም የዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ሥርዓት ተቆጣጣሪ መሆኗን በድጋሚ አስመስክራለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0