የአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል በኢቦላ ቫይረስ ስርጭት ዙሪያ የጤና ሚኒስትሮች ስብሰባ ጠራ

© telegram sputnik_ethiopiaየአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል በኢቦላ ቫይረስ ስርጭት ዙሪያ የጤና ሚኒስትሮች ስብሰባ ጠራ
የአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል በኢቦላ ቫይረስ ስርጭት ዙሪያ የጤና ሚኒስትሮች ስብሰባ ጠራ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.10.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል በኢቦላ ቫይረስ ስርጭት ዙሪያ የጤና ሚኒስትሮች ስብሰባ ጠራ

ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም የሚካሄደው ስብሰባ፤ የኢቦላ ወረርሽኝ በአኀጉሪቱ የጤና ደህንነት ላይ ከባድ ስጋት መደቀኑን እና ናይጄሪያ አዲሱን የቡንዲቡግዮ ዝርያ ተጠቂ መመዝገቧን ተከትሎ የመጣ ነው።

ስብሰባው የበሽታውን ስርጭት ለመገምገም፣ ድንበር ተሻጋሪ ቅንጅቶችን ለማጠናከር፣ ለተጎዱ ሀገራት የሚደረገውን ድጋፍ ለማፋጠን እና የአኅጉሪቱን ዝግጁነትን ለማጠናከር ዕድል እንደሚሰጥ አፍሪካ ሲዲሲ በመግለጫው አመልክቷል።

​“ኢቦላ ድንበር እየተሻገረ ነው። የእኛ ምላሽ በበለጠ ፍጥነት፣ በጠንካራ ቅንጅት፣ በታላቅ አብሮነት እና በቁርጠኛ የፖለቲካ መሪነት መመራት አለበት። በዚህ አኅጉር በቂ ዕውቀት እና አቅም አለን። ይህንን ወረርሽኝ ለማስቆም እና ህይወት ለማዳን እነዚህን አቅሞች ማሰባሰብ አለብን” ሲሉ የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዣን ካሴያ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0