- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የአእምሮ ነፃነት ለፖለቲካዊ መፃኢ እድል እና የፍራንሳፍሪክ አወቃቀር በሳህል ሀገራት መፍረስ

የአእምሮ ነፃነት ለፖለቲካዊ መፃኢ እድል እና የፍራንሳፍሪክ አወቃቀር በሳህል ሀገራት መፍረስ
ሰብስክራይብ
“የቅኝ ግዛት ትምህርት ዋና ዓላማ ነፃ፣ እራሱን የቻለና ተመራማሪ ትውልድን መፍጠር ሳይሆን የቅኝ ግዛት ሀገራትን የሀብት ብዝበዛና አስተዳደር የሚያስፈጽም ታዛዥ መዋቅርን መገንባት ነበር። አፍሪካውያን ታሪካዊ ቀጣይነታቸውን እና የራሳቸውን የአስተዳደርና የእውቀት ፍልስፍና ዳግም ካላረጋገጡ በቀር፣ ከአእምሮአዊ የበታችነት ስሜትና ከፖለቲካዊ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ መላቀቅ አይችሉም።” ሲሉ የየፓን አፍሪካዊ አስተሳሰብ ትምህርት ቤት መስራች እና ዳይሬክተር ናይጄል ስቱዋርት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅታችን፡ በክፍል አንድ፦ የቅኝ ግዛት የትምህርት ሥርዓት በአፍሪካ የፖለቲካ አስተሳሰብና ማንነት ላይ ያሳደረውን ዘላቂ አሉታዊ ተፅዕኖ፣ የሀገር ውስጥ እውቀቶችንና ታሪክን ወደ ትምህርት ገበታ በመመለስ አእምሮአዊ ነፃነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ እና የዲጂታል መድረኮችን ሚና ከፓን-አፍሪካኒስቱ ምሁር ከናይጄል ስቱዋርት ጋር በጥልቀት እንዳስሰዋለን። በክፍል ሁለት፦ በሳህል ቀጠና ሀገራት (ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር) የፈረንሳይ የነዮ-ኮሎኒያል የበላይነት መዋቅር (Françafrique) ስረ-መሰረታዊ መፍረስ፣ የሴኤፍኤ ፍራንክ (CFA Franc) የገንዘብ ጥገኝነት፣ የሳህል ሀገራት ህብረት (AES) ምስረታ እና ቀጠናው ወደ አዲሱ የጂኦ-ፖለቲካዊና የባለብዙ ወገን (Multipolar) አለም አቀፍ ትስስር የሚያደርገውን ሽግግር ከፖለቲካና ኤኮኖሚ ተንታኙ ከካባላ ጆን ጋር ቃኝተነዋል።

ሙሉውን መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0