አዲስ ዙር የሩሲያ፣ አሜሪካ እና ዩክሬን የሦስትዮሽ ድርድር በአቡ ዳቢ ሊካሄድ ይችላል - የፑቲን ረዳት
19:35 21.10.2026 (የተሻሻለ: 19:44 21.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አዲስ ዙር የሩሲያ፣ አሜሪካ እና ዩክሬን የሦስትዮሽ ድርድር በአቡ ዳቢ ሊካሄድ ይችላል - የፑቲን ረዳት
"ዓላማችን አቡ ዳቢ ነው...ይህ በህዳር ወር የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ውስጥ እንዲሆን ተስማምተናል" ሲሉ ዩሪ ኡሻኮቭ ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
አሜሪካ በኦስሎ በተደረገው ድርድር በአውሮፓውያን አካሄድ ላይ "አዲስ ፍንጮች" እንዳስተዋለች፤ ሆኖም አሁንም ሙሉ በሙሉ የሩሲያን ፍላጎት እንደማያሟሉ ገልጸዋል።
ኡሻኮቭ በመግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
ፑቲን በዩክሬን ግጭት መፍትሄ ፍለጋ ላይ ለሚደረገው የሦስትዮሽ ውይይት በሩሲያ በኩል የሚካተተውን የልዑካን ቡድን ይወስናሉ፣
ቭላድሚር ፑቲን፣ ዶናልድ ትራምፕ እና ሺ ጂንፒንግ በቻይና ከሚካሄደው የእስያ-ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ ጎን ለጎን ሦስትዮሽ ውይይት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው አረጋግጠዋል፣
ፑቲን ከዊትኮፍ ጋር ያደረጉት ውይይት፤ በሉኮይል ግዙፍ የነዳጅ ኩባንያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ጨምሮ ዋነኛ የሩሲያ-አሜሪካ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶችን በጥልቀት የዳሰሰ ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X