"ሰንደይ ሞርኒግ" የተሰኘው የኢትዮጵያ አኒሜሽን ፊልም ፕሮጀክት በደርባን ፊልም ፌስቲቫል ሁለት ሽልማቶችን አሸነፈ

© telegram sputnik_ethiopia"ሰንደይ ሞርኒግ" የተሰኘው የኢትዮጵያ አኒሜሽን ፊልም ፕሮጀክት በደርባን ፊልም ፌስቲቫል ሁለት ሽልማቶችን አሸነፈ
ሰንደይ ሞርኒግ የተሰኘው የኢትዮጵያ አኒሜሽን ፊልም ፕሮጀክት በደርባን ፊልም ፌስቲቫል ሁለት ሽልማቶችን አሸነፈ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.10.2026
ሰብስክራይብ

"ሰንደይ ሞርኒግ" የተሰኘው የኢትዮጵያ አኒሜሽን ፊልም ፕሮጀክት በደርባን ፊልም ፌስቲቫል ሁለት ሽልማቶችን አሸነፈ

በናሆም አብይ የተዘጋጀው እና በምናሴ ተረፈ የተመራው ይህ ፕሮጀክት፤ 100,000 የደቡብ አፍሪካ ራንድ (6,106.04 ዶላር) የሚያስገኘውን የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ የፊልም እና ቪዲዮ ፋውንዴሽን ‘የምርጥ አኒሜሽን’ ሽልማት ተቀብሏል።

"ሰንደይ ሞርኒንግ" በተጨማሪም የአኒሜሽን ፕሮዳክሽን ቀናት ሽልማትንም አግኝቷል።

ሽልማቶቹ ይፋ የተደረጉት ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 በደቡብ አፍሪካ ደርባን በተካሄደው 17ኛው የደርባን ፊልም ማርት ማጠቃለያ ላይ ነበር።

በዝግጅቱ ከ56 ሀገራት የተውጣጡ 1 ሺህ 131 የፊልም ባለሙያዎች እና የፊልም ሠሪዎች ተሳትፈዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0