ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ድንበር ተሻጋሪ ውሃዎችን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ድንበር ተሻጋሪ ውሃዎችን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ድንበር ተሻጋሪ ውሃዎችን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.10.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ድንበር ተሻጋሪ ውሃዎችን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ተስማሙ

ኡጋንዳ ከኢትዮጵያ ጋር ቀደም ሲል የተፈራረመቻቸውን ስምምነቶች ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጻለች። ይህ ይፋ የሆነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ ከኡጋንዳ አቻቸው መለስ ሙሊምባ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ነው።

በውሃ ሀብት አጠቃቀም፣ በአየር ንብረት ለውጥና በሽብርተኝነት መከላከል ዙሪያ የሚደረገው ትብብር የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ ለጋራ ልማት እገዛ እንደሚያደርግ አምባሳደር ሃደራ አበራ በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል።

ሁለቱ አካላት በቀጣናው ሰላምና ደኅንነትን ለማስጠበቅ ትብብርን ማሳደግ በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያም መክረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0