የጋና ፕሬዝዳንት የማዕድናትን ሉዓላዊነት ለማጠናከር ከጎርጎሮሳውያኑ 2030 ጀምሮ ጥሬ ማዕድናትን ወደ ውጭ መላክ የሚከለክለውን ውሳኔ ደገፉ
የጋና ፕሬዝዳንት የማዕድናትን ሉዓላዊነት ለማጠናከር ከጎርጎሮሳውያኑ 2030 ጀምሮ ጥሬ ማዕድናትን ወደ ውጭ መላክ የሚከለክለውን ውሳኔ ደገፉ
በአክራ በተካሄደው የ2026 “ማይኒንግ ኢን ሞሽን” ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ፣ አፍሪካ ጥሬ ሀብቷን እሴት ወደ ተጨመረባቸው ምርቶች መለወጥ እንድትችል የተቀናጀ ቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የማቀናበር አቅም እንዲገነባ ጥሪ አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንት ማሃማ በንግግራቸው ያነጠቀሷቸው የጋና ዋና ዋና ጥረቶች፦
▪ ሕገወጥ የማዕድን ማውጣት ሥራዎችን መግታት፣
▪ ጉዳት የደረሰባቸውን መሬቶች መልሶ ማልማት እና
▪ ባህላዊ እና አነስተኛ የማዕድን ማውጣት ዘርፍን በሕጋዊ ማዕቀፍ ማደራጀት።
በመላው ጋና በሕገወጥ ማዕድን ማውጣት ምክንያት ከ4,850 ሄክታር በላይ መሬት መውደሙን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፣ አሁን ላይ ሰፊ የመልሶ ማልማት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። እስካሁንም 323 ሄክታር በላይ መሬት ማልማትና ችግኝ መትከል የተቻለ ሲሆን፣ የጋና ወርቅ ቦርድ ደግሞ ተጨማሪ 102 ሄክታር መሬት የማልማት ሥራ እያከናወነ ይገኛል።
ጋና ሀገር ውስጥ የማዕድን ማቀናበሪያዎችን የመገንባት አቅጣጫን ከተከተሉ እንደ ኬንያ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ እና ዚምባብዌ ካሉት የአፍሪካ ሀገራት ጎራ ተቀላቅላለች። ይህም ማዕድናትን በሀገር ውስጥ በማቀናበር ከፍተኛ እሴት ያላቸውን ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ የተነደፈ ሰፊ ስልት አካል ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X