በሱዳን የተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሲቪሎችን እየገደሉ እና ወሳኝ አገልግሎቶችን እያቋረጡ መሆኑን ተመድ ገለጸ
08:00 21.10.2026 (የተሻሻለ: 08:04 21.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሱዳን የተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሲቪሎችን እየገደሉ እና ወሳኝ አገልግሎቶችን እያቋረጡ መሆኑን ተመድ ገለጸ
የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በሱዳን በርካታ አካባቢዎች የድሮን ጥቃቶች መፈጸማቸውን አስታውቋል፡፡
🟠 ካርቱም፦ ከአየር ማረፊያው አቅራቢያ የተፈጸመ ጥቃት አንድ ሲቪልን በመግደል እና በረራዎች እንዲሰረዙ አስገድዷል፡፡
🟠 ምዕራብ ዳርፉር፣ ቢር ሳሊባ፦ ዘጠኝ ሕፃናትን ጨምሮ 11 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
🟠 ደቡብ ዳርፉር፣ ንያላ፦ ሕፃን ልጅን ጨምሮ ቢያንስ አራት ሰዎች ተገድለዋል፡፡
🟠 ሰሜን ኮርዶፋን፣ አቡ ዘባድ፦ ቢያንስ አራት ሲቪሎች ተገድለዋል፡፡
🟠 ብሉ ናይል ግዛት፣ ኡም ዳርፋ፦ በጤና ጣቢያ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የሱዳን ቀይ መስቀል ማኅበር በጎ ፈቃደኛ ተገድለዋል።
እየጨመረ ያለው የምግብ ዋጋ ጫናውን አባብሶታል።
የሀገር ውስጥ የምግብ ዋጋ ከነሐሴ ወር ጋር ሲነጻጸር በመስከረም ወር 24 በመቶ ጨማሪ አሳይቷል፤ ይህም በገንዘብ ዋጋ መቀነስ፣ በነዳጅ እጥረት እና ከግጭት ጋር በተያያዙ የገበያ መስተጓጎሎች የተከሰተ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X