- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

ታሪክን ማገናኘት እና የወደፊት እጣ ፈንታዎችን መገንባት፡ የሩሲያ-ኢትዮጵያ ግንኙነት እና የባህል ዲፕሎማሲ

ታሪክን ማገናኘት እና የወደፊት እጣ ፈንታዎችን መገንባት፡ የሩሲያ-ኢትዮጵያ ግንኙነት እና የባህል ዲፕሎማሲ
ሰብስክራይብ
“በአፍሪካ ያሉ አብዛኛዎቹ ሀገራት እና ህዝቦች ስለ ሩሲያ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ፤ የሩሲያን አቋምም በተሻለ ሁኔታ መረዳት ይሻሉ። እነሱም አብረዋቸው ሁለቱም ወገን በሚጠቀሙበት የትብብር ስርአት መስራት የሚችል አዋጭ አጋር እየፈለጉ ነው፤ ሩሲያም ለእዚህ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነች።” ሲሉ በአዲስ አበባ የሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን ማዕከል) ዳይሬክተር ቭላዲሚር ቭላዲሚሮቪች ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅታችን፡ በክፍል አንድ፦ የሩሲያ እና ኢትዮጵያን ታሪካዊ፣ መንፈሳዊ እና ባህላዊ ዲፕሎማሲ፣ የትምህርት እድሎችን ፣ የፑሽኪን ማዕከልን ዘመናዊ ሚና እና የሩሲያ የባህል ዲፕሎማሲ በአፍሪካ አህጉር እየሰፋ ያለበትን ስትራቴጂካዊ ሁኔታ ከማዕከሉ ዳይሬክተር ከቭላዲሚር ቭላዲሚሮቪች ጋር በጥልቀት እንዳስሰዋለን። በክፍል ሁለት፦ የአፍሪካን የጤና ሉዓላዊነት ማረጋገጥ እና የክትባት ምርትን በሀገር ውስጥ መጀመር የሚጠይቀውን አህጉራዊ ጥረት፣ የአለም አቀፍ አቅርቦት ሰንሰለት ተጋላጭነቶችን፣ ለሀገር ውስጥ ማኑፋክቸሪንግ የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ፣ የመሰረተ ልማት፣ የፖሊሲ እና የፋይናንስ ማዕቀፎችን ከአለርት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕፃናት ሐኪም እና የሕፃናት ተላላፊ በሽታዎች ሰብ-ስፔሻሊስት ከሆኑት ከዶ/ር ጡረኛ አሰፋ ስዩም ጋር በስፋት ቃኝተነዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0