- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የአፍሪካ ሴታዊንት በአፍሪካ በሥነ ጽሑፍ ውስጥ፦ በባህላዊ ሥር እና በፖለቲካዊ ትግል መካከል

የአፍሪካ ሴታዊንት በአፍሪካ በሥነ ጽሑፍ ውስጥ፦ በባህላዊ ሥር እና በፖለቲካዊ ትግል መካከል
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሥነ ጽሑፍ ‘ሴታዊነት’ን (ፌሚኒዝምን) ከአፍሪካ ታሪክ፣ ከአፍሪካ ተጨባጭ ባህልና ከማኅበረሰባዊ ሕይወት መንጭቶ የወጣ ትግል አድርጎ ያቀርበዋል።
“የአፍሪካ ሥነ ጽሑፍና የራሱ መልክና ቅርፅ ያለው የአፍሪካውያን ሴታዊነት (ፌሚኒዝም) ከጥንት ጀምሮ በባህላችን ውስጥ የነበረ እንጂ ከውጭ የመጣብን አይደለም፤ ምክንያቱም ሥነ ጽሑፍ ነጸብራቅ ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰብን አመለካከትና ባህል የመቅረፅና የማደስ አቅም ያለው ጠንካራ መሣሪያ ነው” ሲሉ በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ መምህር እንዲሁም የማኅበራዊ ሳይንስ እና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ የአፍሪካ ሥነ ጽሑፍ ፌሚኒዝምን ከውጭ እንደመጣ ሐሳብ ሳይሆን በታሪክና በባህል የተቀረጸ ሕይወት አድርጎ እንዴት እንደሚያቀርበው እንቃኛለን። በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ መምህር እንዲሁም የማኅበራዊ ሳይንስ እና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) እንግዳችን አድርገናቸዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0