ጸረ-ተሕዋስያን መድኃኒት የተላመዱ በሽታዎች በኢትዮጵያ እንስሳት ሃብት ልማት ላይ ስጋት ደቅነዋል - የግብርና ባለሥልጣን
21:15 20.10.2026 (የተሻሻለ: 21:24 20.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጸረ-ተሕዋስያን መድኃኒት የተላመዱ በሽታዎች በኢትዮጵያ እንስሳት ሃብት ልማት ላይ ስጋት ደቅነዋል - የግብርና ባለሥልጣን
የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ሰሎሞን ከበደ፣ መንግሥት ችግሩ በከብት ማደለቢያዎች እንዳይከሰት የመከላከል ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝና የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ገቢ ለማሳደግ የእንስሳት እና ተዋጽኦዎቻቸውን ጥራትና ደህንነት የማረጋገጥ ተግባራት እየሠራ መሆኑን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።
"እንስሳትን መድኃኒትን ከተላመዱ በሽታዎች ለመጠበቅ እንደ ክትባት፣ ባዮ ደህንነት እና ቁጥጥር እና ክትትል ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡ በሽታው ቢከሰት እንኳን ሳይዛመት በፍጥነት በቁጥጥር ስር ለማዋል የመድኃኒት አቅርቦትን ማረጋገጥ ተችሏል” ማለታቸውን በስፍራው የተገኘው የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
የግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ጽጌረዳ ፍቃዱ በበኩላቸው፣ የአረንጓዴ አሻራ እና የሌማት ትሩፋት መርሃግብሮች በእንስሳት ሀብት ምርታማነት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ሕገ-ወጥ የእንስሳት እንቅስቃሴን ለመግታት በድንበር አካባቢዎች የቁጥጥር ማዕከላት መቋቋማቸውን አስረድተዋል።
15ኛው የኢትዮጵያ ፖልትሪ ኤክስፖ፣ 11ኛው የአፍሪካ የእንስሳት ሃብት ዐውደ-ርዕይ እና ጉባኤ እንዲሁም 6ኛው የአኳካልቸር ኢትዮጵያ ኤክስፖ ከጥቅምት 19 እስከ 21 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይፋ ተደርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X