ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተሻሻለ የ"ቺያ ዘር"* ሰብል ዝርያ በማመረት ላይ መሆኑን አስታወቀ
20:17 20.10.2026 (የተሻሻለ: 20:24 20.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተሻሻለ የ"ቺያ ዘር"* ሰብል ዝርያ በማመረት ላይ መሆኑን አስታወቀ
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በግብርና ምርምር ማዕከል ያሻሻለው የቺያ ዘር አዲስ ዝርያ ወደ ተጨባጭ ምርት ማሸጋገሩን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተውፊቅ ጀማል ገልጸው፣ ሰብሉም የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።
የዜናው ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 ተኪ ምርት፦ የቺያ ዘር ምርት በኢትዮጵያ ያልተለመደና ከውጭ በከፍተኛ ወጪ ይገባ የነበረ በመሆኑ፣ አዲሱ ሀገር በቀል ምርት የውጭ ምርትን በተኪ ግብርና ለመተካት ትልቅ ሚና ይጫወታል።
🟠 የገበያ ዋጋ፦ አሁን ባለው የሀገር ውስጥ ገበያ ከውጭ ተመርቶ የሚገባ አንድ ኪሎ ግራም የቺያ ዘር እስከ 4,500 ብር ይሸጣል።
🟠 የውጭ ንግድ፦ ምርቱ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመሸፈን ባለፈ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት ታቅዶ እየተሠራበት ይገኛል።
*ቺያ ዘር (ቺያ ሲድ) በውስጡ ከፍተኛ የኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ፣ ፋይበር፣ ፕሮቲን እና አንቲኦክሲዳንት የያዘ ሲሆን፤ ለልብ ጤና፣ ለክብደት መቀነስ እና ለአጠቃላይ ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት ተመራጭ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X