“ስፑትኒክ አዳዲስ ድምፆች እና አዳዲስ ቋንቋዎች ይኖሩታል” — የስፑትኒክ ሚዲያ እናት ድርጅት ሮሲያ ሴጎድኒያ ዋና ዳይሬክተር
19:55 20.10.2026 (የተሻሻለ: 20:04 20.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
“ስፑትኒክ አዳዲስ ድምፆች እና አዳዲስ ቋንቋዎች ይኖሩታል” — የስፑትኒክ ሚዲያ እናት ድርጅት ሮሲያ ሴጎድኒያ ዋና ዳይሬክተር
የመጀመሪያውን የአፍሪካ ቢሯችንን በኢትዮጵያ ከከፈትን ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ዛሬ በታንዛኒያ እና በደቡብ አፍሪካ አዳዲስ የዝግጅት ማዕከሎቻችንን በኩራት እያስመረቅን እንገኛለን ሲሉ ዲሚትሪ ኪሴሌቭ የማዕከላቱን መመረቅ አስመልክቶ ባስተላለፉ የቪዲዮ መልዕክት ገልጸዋል።
“በመላው አፍሪካ ለሚገኙ አዳማጮቻችንና አንባቢዎቻችን የአፍ መፍቻ ቋንቋዎችን እንጠቀማለን፤ የስፑትኒክ አፍሪካ አመሠራረቱ ለአኅጉሪቱ ሰፊ የቋንቋ ብዝኃነት አክብሮት አንዲኖረው ተደርጎ ነው። በእንግሊዝኛ እና በፈረንሳይኛ፣ እንዲሁም በአማርኛ፣ በኦሮሚኛ እና በስዋሂሊ እንሰራለን።”
ለአንድ ወገን ያደላ እና ምዕራባውያንን ብቻ ማዕከል ያደረገ የመረጃ አቀራረብ እየተገፋ በሄደበት በዚህ ወቅት፣ ስፑትኒክ የአፍሪካን ድምጽ በአፍሪካውያን በማሰማት የድምጽ ብዝኃነትን እያጎለበት እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
ስፑትኒክ በአኅጉረ-አፍሪካ ፍትሐዊ የመረጃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት ዋና ዳይሬክተሩ ያቀረቡትን ሙሉ የቪዲዮ ማብራሪያ ከታች ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X