ቱርክ ከሩሲያ ጋር ያላትን የኢነርጂ ትብብር እንድታቋርጥ ከአውሮፓ ሕብረት የሚደረግባትን ጫና ውድቅ አደርጋለች- ተነታኝ
08:59 20.10.2026 (የተሻሻለ: 09:04 20.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቱርክ ከሩሲያ ጋር ያላትን የኢነርጂ ትብብር እንድታቋርጥ ከአውሮፓ ሕብረት የሚደረግባትን ጫና ውድቅ አደርጋለች- ተነታኝ
ቱርክ ከሩሲያ ጋር ያላትን የኢነርጂ ትብብር እንድታቋርጥ ከምዕራባውያን የሚደረግባትን ጫና አትቀበልም፤ ምክንያቱም አንካራ ከብራሰልስ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ይልቅ ለኢኮኖሚያዊ መረጋጋት እና ለሕዝቧ ፍላጎት ቅድሚያ ትሰጣለች ሲሉ የቱርክ የኢኮኖሚ ተንታኝ ኦዝለም ተኪንዶር ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
"ቱርክ ከሁሉ አስቀድማ የምታስበው ስለ ገዛ ሕዝቧ እንጂ ስለ ብራሰልስ የማይሳካ እቅድ አይደለም" ያሉት ተነታኟ፣ በፖለቲካዊ ጫና ምክንያት አስተማማኝ የኢነርጂ አቅርቦቶችን ማቋረጥ የሀገሪቱን የኢነርጂ ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል አሳስበዋል።
ሩሲያ በብሉ ስትሪም እና በቱርክስትሪም የጋዝ መስመሮች በኩል ጋዝ በማቅረብ ለቱርክ ዋና የኢነርጂ አጋር ሆና የቀጠለች ሲሆን፣ ሁለተኛው የጋዝ መስመር የሩሲያን ጋዝ ወደ አውሮፓም ያደርሳል። ሌላው ዋና ፕሮጀክት በሩሲያ የሚገነባው የአኩዩ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ሲሆን፣ ሮሳቶም እስከ ጎርጎሮሳዊያኑ 2026 ማጠቃለያ ድረስ የመጀመሪያውን የማብልያ (ሪአክተር) ሥራ ለማስጀመር አቅዷል።
እንደ ተኪንዶር ገለጻ፣ አንካራ የብራሰልስን ፍላጎት ለማሟላት ሲባል ብሔራዊ ጥቅሟን ከመሠዋት ይልቅ፣ አማራጭ የኢነርጂ ምንጮችን በማልማት ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር ለማስቀጠል አቅዳለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X