- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የአየር ንብረት ፍትህ ለአፍሪካ እና 3ኛው የሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ

የአየር ንብረት ፍትህ ለአፍሪካ እና 3ኛው የሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ
ሰብስክራይብ
መጪው ሦስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ፣ ከጥቅምት 28–29 ቀን 2026 በሞስኮ በሚካሄደው ውይይት በርካታ አጀንዳዎች ላይ ምክክር ያደርጋል። ሀገራት የአፍሪካ አገራት ለዓለም አቀፍ የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀት ያላቸው ድርሻ አነስተኛ ቢሆንም፣ ለከባድ የአየር ንብረት ተፅዕኖዎች የተጋለጡ ሲሆኑ፣ የአየር ንብረት ፋይናንስና ተመጣጣኝ የንጹህ ቴክኖሎጂ ተደራሽነትም ተግዳሮት ሆኖባቸዋል። ጉባኤው ሩሲያና የአፍሪካ አገራት በታዳሽ ኃይል፣ በአየር ንብረት ለውጥ መላመድ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በአቅም ግንባታ ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እድል ይፈጥራል።

''በአየር ንብረት ቀውስ ጉዳይ የበለፀጉ ሀገራት ለተጎጂ ታዳጊ ሀገራት ድጋፎ ማድረግ ይኖርባቸዋል። አፍሪካ አያደገች ያለችና ተስፋ ያላት አህጉር ነች'' ሲሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊሲ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

️በዛሬው ፕሮግራማችን የአየር ንብረት ፍትህ፡ ሩሲያ የአፍሪካን ፍትሃዊ የአየር ንብረት ፋይናንስ እና ንጹህ ቴክኖሎጂ የማግኘት ጥያቄዎችን መደገፍ በምትችልባቸው ሁኔታዎች በተለይም ጉዳዩን ከሦስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ ጋር በማያያዝ ሰፋ ያለ ዳሰሳ እናደርጋለን። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ደግሞ ሙያዊ ዕይታቸውን ያካፍሉናል።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0