- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረክ፦ የአፍሪካ ሕብረት በተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ

አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረክ፦ የአፍሪካ ሕብረት በተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ
ሰብስክራይብ
አፍሪካ የበለጸገ የተፈጥሮ ሀብትና የላቀ የሰው ኃይል አላት፤ በመሆኑም እውነተኛ ስትራቴጂካዊ ነፃነትና ዓለም አቀፍ ተፅዕኖን ለማረጋገጥ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወጥቶ እሴት የመጨመርና የተዋሃደ አህጉራዊ ትብብር ማጠናከርን ይጠይቃል።

"የተፈጥሮ ሀብቱም ሆነ የተማረ የሰው ኃይል አለን። ስለዚህ ስምምነቶቻችን ጥሬ ዕቃዎችን እዚሁ ማቀናበርና እሴት ጨምሮ መላክ ላይ ያተኮሩ መሆን አለባቸው። ይህም የሥራ ዕድል ይፈጥራል፤ ተጨማሪ ገቢንም ያስገኛል" ሲሉ በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ እምቤኪ ኢንስቲትዩት የድህረ-ዶክትሬት ተመራማሪ ቺዶካሼ ንዬሬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዚህኛው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ የአፍሪካ ሕብረትን በንግድ፣ ደህንነት፣ አየር ንብረትና ፋይናንስ ዙሪያ ያለውን ሚና እንፈትሻለን። ሕብረቱ አፍሪካዊ መፍትሔዎችን ወደ ተግባር በላጠበትና አፈጻጸሙ ወደኋላ በቀረበባቸው ጉዳዮች ላይ በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ እምቤኪ ኢንስቲትዩት የድህረ-ዶክትሬት ተመራማሪ ቺዶካሼ ንዬሬ (ዶ/ር) ጋር እንወያያለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0