"ጥሪያችንን ጆሮ ዳባ ማለት አደጋው እጅግ እጅግ ከባድ ይሆናል" - ዐቢይ አሕመድ ኤርትራን አስጠነቀቁ
"ጥሪያችንን ጆሮ ዳባ ማለት አደጋው እጅግ እጅግ ከባድ ይሆናል" - ዐቢይ አሕመድ ኤርትራን አስጠነቀቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ባለፉት 35 ዓመታት እንደታየው ጉርብትና እና ወዳጅነት ብቻ እንደሚያዋጣ ከሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
"ከዚህ ውጪ ያለው አማራጭ አይጠቅምም። የልማት አጋር መሆን ሲቻል የጠላቶች መጫወቻ መሆንን መምረጥ አያዋጣም የሚል እምነት ነው ያለኝ። ጥሪያችንን ጆሮ ዳባ (አለማዳመጥ) ማለት ግን አደጋው እጅግ እጅግ እጅግ እጅግ ከባድ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።”
የኢትዮጵያው መሪ ስለ ኤርትራ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
"ከነጻነት በፊት” የኤርትራ ከተሞች ያበቡና የሸበረቁ ነበሩ፤ ዛሬ ግን የመንደር ያህል ሆነዋል።
አስመራን ከአርባምንጭ ወይም ከጅጅጋ የምታንስ ከተማ ሆናለች።
ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እያለች፤ ከ300 መቶ በላይ ፋብሪካዎች ነበሯት።
በወቅቱ ከአፍሪካ በኢንዱስትሪ ከበለጸጉ ሀገራት አንዱ ተደርጋ ትወሰድ ነበር።
ምጽዋ ባዶዋን ቀርታለች፡፡ አሰብም ተወስዳ ሰው አልባ ከተማ ሆናለች፡፡
የኤርትራ ሕዝብ ከነጻነት በኋላ የነበረውን ሁሉ አጥት ስደት እና እንግልት መገለጫው ሆኗል።
ሕግደፍ (ሕዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ) ልማት እና ተቋማትን መገንባቱን ትቶ የኢትዮጵያ ጠላቶች መሣሪያ ሆኗል።
የኤርትራ መንግሥት አይዞህ ባዮቹም ቢሆኑ ጥይት ከማቀበል አልፈው የኤርትራን ችግር ሊፈቱ አይችሉም፡፡
የራሳቸውን ችግር መፍታት ያልቻሉ አይዞህ ባዮች ለሌላ ሊሆኑ አይችሉም።
የልማት አጋር መሆን ሲቻል የጠላቶች መጫወቻ መሆንን መምረጥ አያዋጣም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X