ዘለንስኪ የራሱን አገዛዝ ለማስጠበቅ ሲል የናፍጣ ስምምነቱን እና የሰላም ንግግሩን ይቃወማል - ሰርጌ ላቭሮቭ
19:48 18.10.2026 (የተሻሻለ: 19:54 18.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዘለንስኪ የራሱን አገዛዝ ለማስጠበቅ ሲል የናፍጣ ስምምነቱን እና የሰላም ንግግሩን ይቃወማል - ሰርጌ ላቭሮቭ
በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የናፍጣ ስምምነት ሙሉ በሙሉ በሞስኮ እና በዋሽንግተን መካከል ያለ ጉዳይ መሆኑን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ገልጸዋል።
የቮሎዲሚር ዘለንስኪን "እኔን ሊያማክሩኝ ይገባል" የሚል ጥያቄ ራስን ከፍ ከፍ የማድረግ ፍላጎት" ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።
በባህሬን ከተካሄደው የሩሲያ-የባሕረ ሰላጤ ሀገራት የትብብር ምክር ቤት የስትራቴጂክ ውይይት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ላቭሮቭ የአውሮፓ ፖለቲከኞች የዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦት መረጋጋትትን እያደፈረሱ በሩሲያ የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ የዩክሬን ጥቃቶችን ይደግፋሉ ሲሉ ከሰዋል።
"ዘለንስኪ የሰላም ንግግር አይፈልግም" ያሉት ላቭሮቭ፤ የሚንስክ ስምምነቶችን፣ በኢስታንቡል እና በአቡ ዳቢ የተደረጉ ንግግሮችን ጨምሮ ድርድሮችን ደጋግሞ አበላሽቷል ሲሉ ወንጅለዋል።
ዘለንስኪ ለማንኛውም ስምምነት ፈቃደኛ የማይሆነው ለሩሲያ እና ለአሜሪካ ተቀባይነት ያለው ስምምነት ላይ መድረስ የራሱ የፖለቲካ ስርዓት ማብቃት ማለት መሆኑን ስለሚረዳ ነው ሲሉ ላቭሮቭ ሞግተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X