በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

© telegram sputnik_ethiopiaበአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.10.2026
ሰብስክራይብ

በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13፣ ወረዳ 1 እና ወረዳ 15 በተለያዩ ሠዓታት በደረሱ ሦስት የትራፊክ አደጋዎች የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በሌሎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

የአደጋዎቹ ዝርዝር፦

ጀሞ ቅዱስ ሚካኤል (ወረዳ 13)፦ ኮድ 3-08136 ኢት ሲኖትራክ ተሽከርካሪ 10 መኪኖችን በመጋጨቱ የ44 ዓመት እናት ሕይወት አልፏል፡፡ 1 ሰው ከባድ እንዲሁም 11 ሰዎች ቀላል የአካል ጉዳት አስተናግደዋል።

ጀሞ ሦስት (ወረዳ 01)፦ ከምሽቱ 12:00 ሠዓት ላይ ኮድ 2A-43228 አ/አ ፒክአፕ ተሽከርካሪ መንገድ ሲሻገር የነበረን እግረኛ ገጭቶ የሰውየውን ሕይወት አልፏል።

ሀጫሉ መንገድ (ወረዳ 15)፦ ከምሽቱ 4:30 አካባቢ ኮድ 3-52305 አ/አ ሀዩንዳይ ተሽከርካሪ ከመንገድ ጠርዝ ጋር በመጋጨቱ የአሽከርካሪው ሕይወት ወዲያውኑ አልፏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopiaበአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.10.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0