አዲስ አበባ ለሚፈጸሙባት ጥቃቶች ምላሽ የመስጠት መብት አላት - የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

አዲስ አበባ ለሚፈጸሙባት ጥቃቶች ምላሽ የመስጠት መብት አላት - የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት ወደ "ሰፊ ግጭት" ሊሸጋገር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ሩቢዮ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት አስተያየት፤ አዲስ አበባ ለሚሰነዘሩባት ጥቃቶች ምላሽ የመስጠት መብት እንዳላት ገልጸው፤ አሁን ዓለም ተጨማሪ ጦርነት ስለማያስፈልጋት በትዕግስት እና ጥንቃቄ አንዲያዝ አሳስበዋል።

የሁለቱ ወገኖች አቋም፦

ኢትዮጵያ ኤርትራ በትግራይ ክልል ላይ "ሁሉን አቀፍ ወረራ" ፈጽማለች ስትል የከሰሰች ሲሆን፤ የኤርትራ ወታደሮች እስከ 60 ኪሎ ሜትር አልፈው ወደ 'ድንበሬ ገብተዋል' ስትል ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት በላከችው ማሳሰቢያ ራሷን እንደምትከላከል አስጠንቅቃለች።

ኤርትራ የቀረበውን ክስ ውድቅ ያደረገች ሲሆን ሀገሪቱ "ያለ አንዳች ቀስቃሽ ምክንያት የተከፈተባት የጥቃት ጦርነት" እያጋጠማት መሆኑን ገልጻ ክሶቹን "ከፍሬ ነገር የጸዱ እና እሳትን የሚጭሩ" በማለት ጠርታቸዋለች።

ℹ ቀደም ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሌክሳንድር አሊሞቭ በሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤም ሆነ በሌላ አማራጭ ለስምምነት የሚሆን የመደራደሪያ መድረክ ለማመቻቸት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ነበር።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0