የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢንቮሽንንና የሰው ኃይል አቅምን ለማሳደግ የአምስት ወገን ዓለም አቀፍ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢንቮሽንንና የሰው ኃይል አቅምን ለማሳደግ የአምስት ወገን ዓለም አቀፍ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢንቮሽንንና የሰው ኃይል አቅምን ለማሳደግ የአምስት ወገን ዓለም አቀፍ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.10.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢንቮሽንንና የሰው ኃይል አቅምን ለማሳደግ የአምስት ወገን ዓለም አቀፍ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በቻይና ዌይፋንግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የሥልጠና መርሃ ግብር ላይ ተሳትፎን ካደረገ በኋላ፣ የመግባቢያ ስምምነቱን ተፈራርሟል።

ኢንስቲትዩቱ፣ "ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ግብ አይደለም፤ ዋናው ግብ ምርታማነትን ማሳደግ ነው" የሚለውን መርህ መሠረት በማድረግ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ከሀገር ውስጥ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስማማት ማምረትና መጠቀም ቀዳሚው ጉዳይ መሆኑን አስረድቷል።

ስምምነቱ፦

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በቼንግዱ የግብርና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል፣ በዌይፋንግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ በዦንግኖንግ ያንታይ ማውንቴን ኢንተለጀንት አግሪካልቸራል ማሺነሪ እና በሻንዶንግ ሊማኦቶንግ ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት መካከል የተፈረመ ነው።

በግብርናው ዘርፍ የዘመናዊ የግብርና መሣሪያዎችና የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በሀገር ውስጥ አቅም ለማሳደግና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማፋጠን ያለመ ነው።

በግብርና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የባለሙያዎችን ዕውቀትና ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ የልምድ ልውውጦችና የስልጠና ዕድሎች ይመቻቻሉ።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0