የግብፁ ፕሬዝዳንት ኤል-ሲሲ በ2030 የሥልጣን ዘመናቸው ከማብቃቱ አስቀድሞ የወደፊት መሪዎችን የማሠልጠን ዕቅዳቸውን ይፋ አደረጉ – መግለጫ
09:30 18.10.2026 (የተሻሻለ: 09:34 18.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የግብፁ ፕሬዝዳንት ኤል-ሲሲ በ2030 የሥልጣን ዘመናቸው ከማብቃቱ አስቀድሞ የወደፊት መሪዎችን የማሠልጠን ዕቅዳቸውን ይፋ አደረጉ – መግለጫ
በግብፅ ወታደራዊ አካዳሚ የምረቃ ሥነ-ሰርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ፤ አካዳሚው የወደፊት ፕሬዝዳንቶችን፣ ሚኒስትሮችን፣ ገዥዎችን እና የፓርላማ አባላትን በማዘጋጀት ረገድ ማዕከላዊ ሚና ሰጥተውታል።
ከንግግራቸው የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፡-
🟠 መርሃ-ግብሩ ለ 30 ወራት የሚቆይ ሲሆን፣ ከታዋቂ የግብፅ እና የውጪ ዩኒቨርሲቲዎች የዶክትሬት (ፒ.ኤ.ች.) ዲግሪ ያገኙ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡
🟠 በፓርላማው አፈ-ጉባኤ የሚመራ ኮሚቴ የመምረጫ መስፈርቶችን የሚያወጣ ሲሆን ሕጎችንም ያረቃል፡፡
🟠 የሕገ-መንግስት ማሻሻያ እንደማይደረግ የገለፁት ኤል-ሲሲ፣ የሥልጣን ዘመናቸው እስከ 2030 መጨረሻ ድረስ "ሙሉ በሙሉ የተወሰነ" (የፀና) መሆኑን ተናግረዋል፡፡
🟠 ግብፃውያን ከዚህ መርሃ-ግብር ተመራቂዎች መካከል መርጠው የመወሰን እድል ይኖራቸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X