የአውሮፓ ልሂቃን የውስጥ ህዝባዊ አመፅ ሊገጥማቸው ይችላል - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaየአውሮፓ ልሂቃን የውስጥ ህዝባዊ አመፅ ሊገጥማቸው ይችላል - ባለሙያ
የአውሮፓ ልሂቃን የውስጥ ህዝባዊ አመፅ ሊገጥማቸው ይችላል - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.10.2026
ሰብስክራይብ

የአውሮፓ ልሂቃን የውስጥ ህዝባዊ አመፅ ሊገጥማቸው ይችላል - ባለሙያ

በራሳቸው ሀገራት ውስጥ ያለው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እየተባባሰ በሄደ ቁጥር የአውሮፓ ሕብረት ባለሥልጣናት ከሩሲያ ጋር የሚያደርጉትን ፍጥጫ እያጠናከሩት ይገኛሉ ሲሉ የጂኦፖለቲካ ተንታኙ ኤንሪኬ ኻቪየር ሬፎዮ አሴዶ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

"ይህ ሁኔታ በዚህ ከተቀጠለ ሥልጣን ላይ ያሉት ልሂቃን ጦርነት ሊያስነሱ ይችላሉ፤ ነገር ግን ጦርነቱ እነሱ የሚመኙት ሳይሆን በእኛ አውሮፓውያን ሀገራት ላይ ባመጡት መከራ እና ችግር ምክንያት በራሳቸው ላይ የሚነሳ ህዝባዊ አብዮት ይሆናል" ሲሉ አብራርተዋል።

አስቸጋሪው ሁኔታ እና ሩሲያን አጋንንታዊ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረጉ ሙከራዎች በአውሮፓ በሚገኙ ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ ህዝቡ ያለው እምነት እንዲሸረሸር እያደረገው መሆኑን ሬፎዮ አሴዶ ጠቁመዋል።

"እዚህ ያለውን ሕይወታችንን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደ እንዲሄድ እያደረጉት ነው፤ ከዚያም በላይ ደግሞ ከሀገር ውጭ ወዳለ ጦርነት ሊጎትቱን ይፈልጋሉ። ይህ ምን ዓይነት አማራጭ ነው? በችግር መኖር እና በፍጥነት መሞት?" ሲሉ ተንታኙ አጠይቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0