- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

ከእግራችን ስር ያለው ህይወት፡ ቴክኖሎጂ እንዴት የኢትዮጵያን አፈር ሊታደግ ይችላል?

ከእግራችን ስር ያለው ህይወት፡ ቴክኖሎጂ እንዴት የኢትዮጵያን አፈር ሊታደግ ይችላል?
ሰብስክራይብ

አፈር ህይወት ነው። ምክንያቱም ህይወት ያላቸው ነገሮች በሙሉ አፈር ውስጥ ነው ያሉት - በየኛ ሀገር ሁኔታ የኬሚካል ማዳበሪያዎች ጉዳት የሚያደርሱበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል ማለት አንችልም። ምክንያቱም በትንሹ ነው እየተጠቀምን ያለነው ከአርሶ አደሩ አንፃር - ሲሉ አለሙ ሌላጎ (ዶ/ር)፣ በወላይታ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ሳይንስ እና ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ከአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ አብራርተዋል።

☀️ ሁለት ወሳኝ ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፦

🌾 በክፍል አንድ፦"ከእግራችን ስር ያለው የተሰወረ ህይወት" በሚል ርዕስ የአፈር ብዝሃ-ህይወት ለምግብ ዋስትና ያለውን ወሳኝ ሚና፣ የኬሚካል ማዳበሪያዎች አጠቃቀምን እና የኦርጋኒክ አፈር እንክብካቤን ከሳይንሳዊ መረጃዎች ጋር እንዳስሳለን። ዶ/ር አለሙ ሌላጎ ዕይታቸውን እና ሙያዊትንተናቸውን ያጋሩናል።

🏥 በክፍል ሶስት፦"አገራዊ የጤና ክፍተቶችን በተስማሚ ቴክኖሎጂዎች መፍትሄ መስጠት" በሚለው ርዕሳችን ደግሞ ውድ የውጭ ቴክኖሎጂዎችን ከመጠበቅ ይልቅ ከአካባቢ ሁኔታ ጋር የተጣጣሙ (Appropriate Technologies) መፍትሄዎችን ማሰራጨት ስላለው ፋይዳ እንነጋገራለን። ዶ/ር ሞላልኝ ቢተው፣ በዘርፉ ረጅም ልምድ ያላቸው ተመራማሪ ሀሳባቸውን ያካፍሉናል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0