የሩሲያ የትምህርት እድል "ልዩ፣ እሴት ያለው እና ድንቅ ዕድል" ነው - የታንዛኒያ ፖለቲከኛ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ የትምህርት እድል "ልዩ፣ እሴት ያለው እና ድንቅ ዕድል" ነው - የታንዛኒያ ፖለቲከኛ

በዓለም ዙሪያ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የትምህርት ፕሮግራም "በአብዛኛው ተመሳሳይ" ቢሆንም፤ ሩሲያ ግን "አንድነትን፣ አብሮ መኖርን፣ የእርስ በእርስ መከባበርን፣ ፍቅርን እና ራስን ከሌሎች አብልጦ አለመመልከትን የሚያጎላ ኮትኩቶ የማሳደግ ባህልን ታቀርባለች" ሲሉ በሩሲያ ለ11 ዓመታት በኢንጂነሪንግ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ቤነሊዝ ማሄንጌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች "ቁጥራቸው በርካታ እና እጅግ በጣም ጥሩ" መሆናቸውን የገለጹት ማሄንጌ፥ ሀገሪቱ በርካታ "ስም ያላቸው ታዋቂ ተቋማት" እንዳሏት አጽንኦት ሰጥተዋል።

በሩሲያ ትምህርታቸውን ለመከታተል እንዴት እንደበቁ ሲያብራሩ፤ ማሄንጌ "ከጎሳ፣ ከጂኦግራፊያዊ ቀጣና ወይም ከክልል" ልዩነት ሳይደረግ እኩል ዕድል ይሰጥ የነበረውን የታንዛኒያ ከነፃነት በኋላ የነበረውን የትምህርት ስርዓት አመስግነዋል።

"ዕድሎች እኩል ይቀርቡ ነበር፤ እኔም በሩሲያ ለመማር ለነበሩት ክፍት ቦታዎች ለማመልከት ደፈርኩ።"

የሩሲያን ባህል እና ቋንቋ መረዳት "በዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና በሥራ ዕድሎች" ውስጥ ትልቅ በር እንደሚከፍት አብራርተዋል።

የሩሲያ የትምህርት ሥርዓት ከምዕራባውያኑ ጋር ሲነጻጸር ምን ይመስላል? የበለጠ ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0