አዲስ አበባ ከፍተኛ በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎችን በካሜራ በመለየት እርምጃ ልትወስድ ነው

ሰብስክራይብ

አዲስ አበባ ከፍተኛ በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎችን በካሜራ በመለየት እርምጃ ልትወስድ ነው

 

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከፍተኛ በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለው መመሪያ ከወጣ በኋላ የተሰጠው የእፎይታ ጊዜ ያበቃ በመሆኑ አሁን ሙሉ በሙሉ ወደ ሕግ ማስከበር እርምጃ እንደሚገባ አስታውቋል።

 

የቢሮው መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦

 

በናሙና ከተፈተሹት 89 የናፍጣ (ዴዝል) መኪኖች ውስጥ መስፈርቱን ያሟሉት 14.6% (13ቱ) ብቻ ናቸው። የቤንዚን መኪኖች ግን 91% አሟልተዋል።

 

ከፍተኛ በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች በቀጣይ በካሜራ ቴክኖሎጂ ተለይተው ከትራፊክ አገልግሎት ይታገዳሉ።

 

አሮጌ መኪኖችን በኤሌክትሪክ እና ንጹህ ተሽከርካሪዎች ለመተካት መንግሥት ከ85% እስከ 90% የሚሆነውን ወጪ በብድር የሚያመቻችበት አሰራር ተዘርግቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0