ግብፅ ጥያቄ ከቀረበላት ሳዑዲ አረቢያን ለመጠበቅ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ናት - ፕሬዝዳንት ኤል-ሲሲ

© telegram sputnik_ethiopiaግብፅ ጥያቄ ከቀረበላት ሳዑዲ አረቢያን ለመጠበቅ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ናት - ፕሬዝዳንት ኤል-ሲሲ
ግብፅ ጥያቄ ከቀረበላት ሳዑዲ አረቢያን ለመጠበቅ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ናት - ፕሬዝዳንት ኤል-ሲሲ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.10.2026
ሰብስክራይብ

ግብፅ ጥያቄ ከቀረበላት ሳዑዲ አረቢያን ለመጠበቅ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ናት - ፕሬዝዳንት ኤል-ሲሲ

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል-ሲሲ ሳዑዲ አረቢያን ከውጭ ጠላት ጥቃት ለመከላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲያጸድቅ የሀገሪቱን ፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ማዘዛቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የግብፅ ፓርላማ ለሳዑዲ የሚደረገውን ድጋፍ አስመልክቶ ነገ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ምት አስቸኳይ ስብሰባውን ያደርጋል፡፡

ግብፅ እና ሳዑዲ አረቢያ "የአረብ እና የእስልምና ዓለማት እምብርት" ላይ የሚገኙ መሆናቸውን እና በየትኛውም ወገን የሚደርስ ጉዳት በሌላው ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ የሁለቱ ሀገራት እንዲሁም የባህረ ሰላጤው አረብ ሀገራት ብሔራዊ ደህንነት እርስ በርስ የተሳሰረ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ግብፅ የሳዑዲ ደህንነት ወይም ድንበር ላይ የሚፈጸም ማንኛውንም ጥሰት፣ እንዲሁም በቀይ ባህር ወይም በዓለም አቀፍ የባህር ማጓጓዣ መስመሮች ላይ የሚሰነዘር ምንም አይነት አደጋን ፈጽሞ እንደማትታገስ አረጋግጠዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0