ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ወታደራዊ ማርሽ ባንዶች ውድድርና ፌስቲቫል ልታስተናግድ ነው
15:25 17.10.2026 (የተሻሻለ: 15:34 17.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ወታደራዊ ማርሽ ባንዶች ውድድርና ፌስቲቫል ልታስተናግድ ነው
አኅጉራዊው ፌስቲቫልና ውድድር ከታህሳስ 2 እስከ 5 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ የመከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
መርሐ ግብሩን የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን፤ ከሁሉም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የተወጣጡ ወታደራዊ ማርሽ ባንዶች ይሳተፉበታል።
ውድድሩ የሚከተሉንትን ያካትታል፦
▪ የጎዳና ላይ ሰልፍ፣
▪ የሜዳ ላይ ትርኢት እና
▪ የልዩ ሙዚቃዎች ውድድር
አዲስ አበባ ይህን አኅጉራዊ መርሃ ግብር በብቃት ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጅት ማድረጓ የተገለጸ ሲሆን ወታደራዊ ባንዶች ባህላቸውንና ትውፊታቸውን የሚያስተዋውቁበት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ተገለጿል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X